Ebake cafe bar and restaurant

Directions

Ebake cafe bar and restaurant Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ebake cafe bar and restaurant, Cafe, Addis Ababa.

23/09/2026
22/08/2026
22/08/2026
22/08/2026

TikTok | Make Your Day

22/07/2026
03/07/2026

የተሰረቀው ወርቅ እና የተተካው ናስ
(በሮሜ 8:34 ላይ የተፈጸመው አስደናቂ የትርጉም ሴራ)

​በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
አሜን🙏🙏🙏

​በክርስቶስ ደም የተዋጃችሁ በወንጌል ብርሃን የበራችሁ የቅድስት ተዋሕዶ እምነታችን ፍሬዎችና የዚህ ገጼ ወዳጆች ማኅበረሰቦች የልዑል እግዚአብሔር ሰላም ጥበቃና ጸጋ በያላችሁበት እንደ ሰማይ ከዋክብት ይብዛላችሁ።

​ዛሬ እንደ አንድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አገልጋይነቴ በመንፈሳዊው ዓለም ውስጥ እጅግ ስውር በሆነ መንገድ እየተሰራጨ ስላለውና የብዙዎችን ነፍስ በስውር ስለሚመርዘው አንድ ትልቅ ምስጢር አብረን እንድንነጋገር ወደድኩ በምሳሌም እያዋዛን እንድንረዳው ይህንን መልእክት ይዤላችሁ ቀረብኩ በፀሎታችሁ አስቡኝ።

​ወዳጆቼ አንድ ገበሬ ምርጥ የስንዴ ዘር ዘርቶ ሳለ ጠላት በሌሊት መጥቶ በስንዴው መካከል እንክርዳድ ቢዘራበትና ፍሬው ሲበቅል መልኩ ቢቀየር እንዴት ያዝናል? ዛሬም በቅዱሳት መጻሕፍት ትርጉም ላይ እየሆነ ያለው ይኸው ነው ።

​በተለይ በሮሜ 8:34 ላይ ያለውን ታላቅ የመለኮት ኃይል ቃል በጥቂቱ እንቃኘው

​የወርቁና የናሱ ምሳሌ በጥንታዊውና በታማኙ የግዕዝ ቅጂያችን ላይ ክርስቶስ ፍርድን የሚሰጥ ልብን የሚመረምር “የሐትት ለልብነ” የባሕርይ አምላክ መሆኑ ተጽፏል ነገር ግን ከ1611 ዓ.ም የኪንግ ጄምስ (King James) ትርጉም ተነስተው ምዕራባውያን በረቀቀ መንገድ ቃሉን “ይማልዳል” ወደሚል የፍጡር ተግባር ቀይረውታል ይህ ማለት ወርቁን ጥለው ናስ እንደማልበስ ይቆጠራል።

​የማጽደቅና የመኮንን ምስጢር ታላቁ ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ “የሚኮንን ማነው? የሞተው ይልቁንም ከሙታን ተለይቶ የተነሳው ክርስቶስ ነው” ሲል ማጽደቅና መኮንን የፈራጅ ሥራ እንጂ የማማለድ ሥራ እንዳልሆነ በግልጽ ያስረዳል እነርሱ እንደሚሉት እርሱ ምድር ላይ ሆኖ የሚለምን ሳይሆን በግርማ በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ እንደ ሥራችን የሚከፍለን እውነተኛ ፈራጅ ነው።

​የሊቃውንቱ አባቶቻችን ጩኸት የሐዲስ ኪዳን ትርጓሜ መምህራን ደጋግመው እንደሚያስጠነቅቁን የክርስቶስን ሙሉ አምላክነትና ከዓብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ያለውን መስተካከል ለመረዳት ወደ ጥንታውያኑ የግዕዝ የሶርያና የኮፕት ቅጂዎች መመለስ ግድ ይለናል።

​የተወደዳችሁ የክርስቶስ ቤተሰቦች ምንጭ ሳይደፈርስ ከቀደመው ዐለት የተቀዳ ውሃ ሁልጊዜም ሕይወት ይሰጣል እኛም ከውጭ በሚመጡና ቃላትን በጥበብ በሚያጣምሙ ስብከቶች ሳንወሰድ የቀደሙት ሊቃውንት አባቶቻችን ያቆዩልንን ጽኑና ኦርቶዶክሳዊ ትርጓሜ ልንመረምርና ልንጠብቅ ይገባል።

​ልዑል እግዚአብሔር ማስተዋሉን ይስጠን ከስውር ስሕተትና ከትርጉም መዛባት በቅዱስ እጁ ይጠብቀን ይህ እውነት ለብዙዎች መዳንና ከእንቅልፍ መንቃት ምክንያት ይሆን ዘንድ እባካችሁ መልእክቱን Share በማድረግ ወንጌላዊ ግዴታችሁን ተወጡ ሃሳብና አስተያየታችሁንም እንዲሁም ጥያቄያችሁን በኮመንት አጋሩኝ

​የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት የቅዱሳን መላእክት ጥበቃና የጻድቃን ጸሎት ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን🙏🙏🙏

​ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር
አሜን🙏🙏🙏 ይቆየን🙏🙏🙏

24/06/2026

‼️

በአዲስ አበባ ጎሮ ኪዳነምህረት አካባቢ መንገድ ላይ ብቻውን ጠፍቶ የተገኘን አንድ ህጻን ልጅ ደጋግ ግለሰቦች አግኝተውት በጥሩ ሁኔታ እየተንከባከቡት ይገኛሉ።

በአሁኑ ሰዓት የህጻኑ እናትና ወላጆች በከፍተኛ ጭንቀትና ሃዘን ላይ እንደሚሆኑ ስለሚገመት፣ ይህንን መረጃ የምታዩ ሁሉ የበኩላችሁን ሰብአዊ ግዴታ በመወጣትና መረጃውን በስፋት ሼር (Share) በማድረግ የህጻኑን ቤተሰቦች በአስቸኳይ እንድናፋልግ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

ለመልካም ስራ መቼም ቢሆን አይረፍድምና ሁላችንም አጋርነታችንን እናሳይ።

የህጻኑን ወላጆች ወይም ህጻኑን የሚያውቅ ማንኛውም የቅርብ ሰው ካለ በጎሮ ፖሊስ ጣቢያ ስልክ ቁጥር 0116661600 ላይ በመደወል ወይም በአካል በመገኘት መረጃ እንዲሰጥ በአክብሮት ተጠይቋል።

ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም"
Via ባይሽ_ኮልፌ

#አፋልጉን #ጎሮ

ጉርሻ Page

🌴🌴🌴

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ebake cafe bar and restaurant posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category