26/10/2017
የልብ ጉዳይ ነው !!!
ይሄ አረማ የተቀባው በሕዝብ ፍቅር የሃገሪቱን ስም ከፊት
ለፊት አስቀምጦ ኢትዮጵያ ተብሎ ቡና የተባለ ብቸኛው
ሃገራዊ ቃና ተላብሶ በኢኮኖሚው ዋልታ ኩራት የሆነ
ለሃገራችን ኢትዮጵያ ‘ ቡና ገበያ ዋልታ ብቻ ሳይሆን ተስፋም
ነበረ ፣ ስሙ ስሙኝ እናንተ አይደላችሁም የንጋት ኮከብን
ቅድማያቶቻችሁ እንኳን እነዛ ፌክና ኮፒ አርበኞች ነን ባዮቹ
ለባንዳ እንቁላል የቀቀሉቱ ቡና ገበያን ሊያፈርሱት አልቻሉም
በምንም መልኩ ቢመዘን አዲስ ቢራ የተባለ የግለሰቦች
መፈንጫ የሆነ ክለብ ኢትዮጵያ ቡናን በምንም አቅም
ሊበትኑት ብዙ ቢጠሩ ብዙ ቢለፉ አያቶቻችሁ ከእዚህ ህዝባዊ
መንፈስ ጋር መታገልና መቋቋም አልቻሉም ምክንያት
ህዝብ አይሸነፍም
የሃገር ውስጥ ዋንጫ ደርድራችኃል
የአፍሪካን ሜዳ ያልተሳለማችሁት የለም
ብዙ ገንዘብ ያላቸው ግለሰቦች ይዛችኋል
የ 81 ዓመት የሽፍታ ታሪክ በአበባ ጃንሆይ ሜዳ ብቻ
ይሄ ሁሉ ሆኖ ዛሬ የሚወለዱት ጨቅላ ህፃናት ፣ ወጣቱ
ጎረምሳው ፣ ጎልማሳው ከ 81 ዓመት የጀዘበ ታሪክ የ ፵
ዓመት ጣዕም ያለው ፍቅር ነፍሳቸውን ማረከው ያለ ዋንጫና
ድል ማሊያውን እየሳመ በቡና ገበያ የዜማ ሽታ እየተማረክ
ካቦሎጆን አስጨነቀው በእድሜወ ያየው ዋንጫ ከሁለት
በማይበልጥ ይሄ የቡና ደጋፊ እንደ ሰማይ ከዋክብት ደምቆና
በዝቶ ታይቷል ደግሞ እንዳማይቆጠር እንደ ምድር አሽዋ
በሜዳው ላይ በቡኒው በቀለም ፈሰሰሰሰ በዛ
ቅኔ ነው ደጋፊው
ሚስጢር ነው ዜማው
እምነት ነው አረማው
ተሰሙኛላችሁ የቡናውን ቀፎ አተንኩት ከትላንትና ተማሩ
በተራ ሐሜት በአሎባለታ የምንተወው ክለብ አይደለም
ለእዚህ ምስክር ነው ጫንያለው ተኮላ የንጋቱ አብሳሪ የነብስ
ነው ኪዳኑ መሃለው በዱላና በፀብ አይደለም በሞት ነው
መሃላችን ፣ ጀግና ነው የሰጠን በመከራው ምጥ ወልዱ ፍቃደ
ማሞ በቡናው ሴክተር በቡናው ማሳ በፍቅር ውኃ እያሳደገ
በሕዝብ ልሳን እያሰጨፈረ የግሪሳዎቹ ጦር እየመከተ
ተንኰልና ምቅኝነቱን እያሳለፈ ቼንቶ ነው የሰጠን ከቡናው
እርሻ ለቅሞ አጥቦና ቀሽሮ ደረጃ አንድ የእኛ ቡና ፣ እንኪያሰ
አሜሪካ ሄዶ ዶራል አያቀንም በራሳችን ለራሳችን የቆምን
የከተማዋን ትልቅ ክለብ በሕዝብ ልብ እንዲወደድ ታገለ
እንጂ ... ፻ አለቃ
ለሆዳቸው ባደሩ ተርጓሚያን ጋዜጠኞች ሐሜት ሞግዚት
የሆነው ፌዴሬሽናችሁ ጉልበት ፣ በብዙ የመሐል ዳኞች
በደልና ጭቆናችሁ ይሄ ሁሉ ያልሰበረው ሕዘብ በስታዲየም
ወንበር ነቀላና ውርወራ የሚበተን ይመስላችኋል ? የፀጥታ
ኃይል ወፍራሙ ዱላ ጅራባችን የለመደው ነው እኛ የጥይት
ጋጋታ የባሮድ ሽታ ያልበተነን ለለበስነው ክብር ማሊያ
ለመሞት የማልን ነን ለእዚህ የአንቦ ሜዳ ፣ አዳማ
ትመስክር ፣ ፊንጫ የሸንኮራው ሜዳ ቃል ያውጣና ይናገር
የአፄዎቹ ሜደ የቴዎድሮስ ሐገረ ፵፬ ቱ ታቦት ይመስክር
ጥይት ማሃል የጨፈርን በድንጋይ ጋጋታ ውስጥ ማሊያ
ያለወለቅን ጀግኖች ነን የቡንዬ ልጆች
ዛሬም ወደኋላ የለም እንደ ማልነው በቃሉ እስከ መሞት
ድረሰ ነው ኪዳናችን ጀበናውን ትቶ የሚያፈገፍግ የፈራ ልብ
የለንም ሚስማር ላይ ነው ህይወታችን ካታንጋ ነው ልባችን
ያለው የትላንት ነን ዛሬ አዲስ ነገር የለንም በቀኝ ጥላ ፎቅ
ነን ታምነን በዜማ ወደ ኋላ የለም ማንም ምንም ቢል ይሄ
ነው ፅናታችን ማሃላችን ከነ ዱርዬነታችን እነሆ ለዘላለም
ነው ቃልኪዳናች ይሄ ነው ኢትዮጵያ ቡናችን
የንጋት ኮከብን ባላሰብ
ቡና ገበያን ብተወው
ኢትዮጵያ ቡናን ብረሳ
ቀኜ ትርሳኝ !!!
Yaredo YaYa
ያያ ኮፊ
ከተመችህ ሼር አድርገው ....