MSYM treading PLC

MSYM  treading PLC Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from MSYM treading PLC, Coffee shop, Addis Ababa.

29/08/2025

ሠርገኛው ከቀናት በኋላ የሚደገሰውን ሰርግ በማስመልከት ዘመድ ወዳጅን በሙሽሪት ቤት ከቷል። ወይዛዝርት ሽንኩርት እየላጡ ሰፋፊ መዘፍዘፊያ ውስጥ ይዶላሉ። ወንዶች ድንኳኑን “ያዝ ያዝ” እየተባባሉ መሬቱ ላይ ይተክላሉ። ግቢው እጅግ ሰፊ ስለሆነ ሁሉንም ነገር ለማድረግ እንደልብ ይመቻል ። ጉሽ ጠላውን እየቀዱ ለዘመድ ለወዳጅ የሚያቀምሱ እና ጣእሙን የሚፈትኑ ወይዛዝርትም በጠላ ጋኑ እና በሠርገኛው መሀል ሸማኔ እንደሚደውረው ዘሀና እና ማግ በሰፊው ግቢ ከወዲህ ወዲያ ውር ውር ይላሉ።
“ቆንጆ ጠላ እቴ!” የሚላቸው ሲበዛ ለስራቸው የተሰጠ ልከኛ ሙገሳ መሆኑን ለማረጋገጥ ሠርገኛውን እያስማሉ እና እያስገዘቱ ምሽቱ ቀጠለ።
ቦታው ሽሮ ሜዳ ሰፈር ቢሆንም ሠርገኛው ከከተማ ከገጠር የመጣ ስለሆነ ጉራማይሌ አለባበስ እና ጨዋታ ጎራ ጎራ ፈጥሮ ይስተዋላል። ከሱሉልታ የመጡት የፈረስ ጉግሰኞች የፈረሱን ልጓም እና ኮርቻቸውን በተለያዩ ቀለም በተሰሩ ልብሶች አስወበዋቸውል ። መጀመሪያ ጊዜ እነዚህ ፈረሶች ሰርግ ወደ ሚደገስበት ቤት እኒህ ፈረሶች ሲመጡ የሰፈሩ ህጻናት ጎረምሶች እየተግተለተሉ ለማየት መጡ። በለፈረሶቹ ዘና ብለው ስለፈረሱ ስለኮርቻው ስለባህሉ አግባብ አስረዷቸው። ከሱሉልታ የያዙትን ቅቤ እና አይብም በክብር ለወይዛዝርቱ አስረከቡ ። ዶርዜዉ ሰርገኛዉም ሸማ ያስመርጣል። የአባይ ማዶዎቹ ደግሞ ማራቸውን ጠጅ ሊያደርጉ ደፋ ቀና ይላሉ። “ጠጅ ዙሪያ ያልሰከነች ሴት ካለች መላ የለውም” እያሉ ከጠጁ እንስራ ማንም እንዳይደርስ ወደ ሰርቢሱ ሰው ዝር እንዳይል ያባርራሉ። ጋን ሙሉ ድፍድፍ ተቀምጦ በጥንቃቄ በገንቦ እየተቀነሰ ጠላ ይዘጋጃል። አገልግል ሙሉ ስንቃቸውን የያዙት ዶሮ ፍትፍት በአፍ በአፍ እየተጎራረሱ ስራውን ያለእረፍት ያሳልጡታል።
እዚህ ቦታ የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ሳያስመለክት የመንግስትም ሆነ የግል ሚድያ ሳይጠራ ኢትዮጵያዊነት ፈገግ ብሏል፤ ምን አልባትም ስለዚህ የተሰባጠረ የባህል ጉራማይሌ ፖለቲከኞች ቢያዩ የእኛ የስራ ውጤት ነው ይሉ ነበር።
ማጀቱ ስር ከሚርመሰመሰው እቃ እና ቦታ ከሚያበጃጀው ይልቅ ድንኳኑ አካባቢ የተሰበሰበው ሰው እየበዛ መጣ። ከዋናው ቤት ራቅ ብሎ የተጣለው ድንኳን አካባቢ ከፍ ብሎ በሚወጣው የዘፈን ድምጽ የተሳበ ሰው ቀስ በቀስ በረከተ። ሙሹሮቹ እና ሚዜዎቹ ከሰርጉ በፊት የነበረውን ቅድመ ዝግጅት ጭፈራ በሰርግ ወረድ እና ቁመት ተያይዘውታል። ከበሮውን ይደልቁታል አንገታቸውን እያርገፈገፉ እስክስታውን ያስነኩታል።
ሲያሻቸው በጉራጌኛ መሬቱን ይተመትሙታል። በኦሮምኛ ጭፈራ እያሻቀቡ በትግረኛ ዘፈን ደርባባነቱን ይመልሱታል። መቼም የኢትዮጵያ ባህላዊ ውዝዋዜዎች ተውጣጥቶ መሀል ሀገር ሲደርስ በሚያስቅም በሚያሳዝን መልኩ መበረዙ አይቀርም። በአብዛኛው ባህሉን የሚያውቀው ወይ በብሽቀት ወይ ላስተምህሮት መድረኩን መቀላቀሉ ከዛም አልፎ ዝም ብሎ የሚወራጨውን ዳር ማውጣቱ አይቀሬ ነው።
ባለ ቱባ ባህሉም፤ ብርዝ ጭፈራውም፤ ባህል ዘመናዊም በለመደው በሚችለው መለስ ቀለስ እያለ እየጨፈረ የቅድመ የድግስ ድባቡ ዘለቀ።
በዚህ ሁላ መሀል ማርታ የሚዜነቷን ለመዋጣት ከዘፈኑ ዜማው ስልተ ምት ጋር ለመዋሀድ ወዝ ወዝ ትላለች። ሙሽሪቷ ሰላም ቀበና ሰፈር አብሮ አደግ ከፍ ሲልም ኮሜርስ አብረው ተምረው የጨረሱ ናቸው። ታዲያ የሰላም ቤተሰቦች ቤት ሸጠው ሽሮሜዳ መኖር ሲጀምሩ ጓደኝነታቸው ያለ አንዳች ሳንካ ቀጠለ። የምታደርገው ለሷ እንኳን ግር እያላት ስንቴ ጭፈራውን አቋርጣ ትወጣለች። መቀነቴ አደናቀፈኝ፤ ምክንያቶቿን እየደረደረች ከዳር ትታደማለች ከማይጨፍሩትም ከማይሰሩትም።
ከዳር በምትሆንበት አፍታዎች እብሽ ድንቁን በቅናት እያየች ለራሷ ደጋግማ አንድ ጥያቄ ትጠይቃለች።
‘ሠርግ ይሄን ያህል ታላቅ ክስተት ሆኖ ነው?’
ከራሷ ጋር የሀሳብ ጨዋታ መሰል ሙግቷን ቀጠለች፤
‘ሠረገ ስንል ድግስ ደገሰ እያልን ነው ወይስ ስለመስረግ መስረጽ እያወራን ይሆን ወይስ መጥፋትን ደግሰን እያከበርን ይሆን?’
ሠርግንም ከሠርግ ጀርባ ያለውን ጥምረት በሀሳቧ ማጥላላቷን ቀጠለች።
‘እንደውም’ አለች በአንድ ወቅት ባይሎጂ ላይ የቃረመቻትን ቃል ነጥላ ተፈጥሮአዊ መጠፋፋት ‘ኦቶሊስ ይሆን እንዴ?’
መቼም የሰው ልጅ ከሱ የራቀ እና ተንጠራርቶ የማይደረስ የሚመስለውን ነገር ሲጋፈጥ የማይፈጥረው የህይወት ፍልስፍና የለም። አሁን ማርታ ሰርግ እስከግሳንግሱ ፊት ለፌት ሆና በጓደኛዋ ሙሽሪት በኩል ተጋፍጣለች። እናም መራር አድርጓታል።
ለወትሮው ማርታ ለሰዎች መልካም የምታስብ፤ የሰው ደስታ የሚያስደስታት፤ የሰው ሀዘን ልቧን የሚነካት ነበረች።
ዛሬ ፌሽታው ሰምታ ከምታውቀው ጩኸት በላይ ረብሿታል።

29/08/2025
23/03/2025

for the coffee lovers

18/12/2024
07/11/2024
የወለጋ ቡና በእጃችን አለ ለመደብርዎም ለሱቅዎም ለካፌዎም በጅምላ እናቀርባለን ።
24/10/2024

የወለጋ ቡና በእጃችን አለ ለመደብርዎም ለሱቅዎም ለካፌዎም በጅምላ እናቀርባለን ።

የኢትዮጵያ ባህላዊ አቆላል traditional coffee roast
19/10/2024

የኢትዮጵያ ባህላዊ አቆላል traditional coffee roast

16/10/2024

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when MSYM treading PLC posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category