NAFMA Coffee

NAFMA Coffee Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from NAFMA Coffee, Coffee shop, Jemo mikael, Addis Ababa.

23/11/2025

በማርበርግ ቫይረስ የተጠቃ ሰው ኑዛዜ እና አፈጻጸሙ
የኢትዮጵያ የውርስ ሕግና ማርበርግ ቫይረስ

ጠበቃና የህግ አማካሪ ፋንታሁን ደለለው 0929101037,0983337690

መግቢያ
| በኢትዮጵያ የውርስ ህግ መሠረት የሟች ሀብት ወራሾች በኑዛዜም ሆነ ህጋዊ ወራሾች በመሆናቸው የሟችን ሀብትን የሚወርሱ ሲሆን
በዚህ ጽሁፍ በማርበርግ ቫይረስ የተያዙ ሰወች ኑዛዜ ማድረግ ቢፈልጉ በሽታው በጣም ተላላፊ እና አስፈሪ ከመሆኑ የተነሳ ሰወች ምስክሮች ቀርበው በተናዛዡ ወይም ተናዛዡ ኑዛዜውን እየተናገረ በሌላ ሰው ተጽፎ ምስክሮች ፈርመው ተግባራዊ ለማድረግ እጅግ በጣም ከባድ ይሆናል። በህጋችን ሶስት አይነት ኑዛዜ የሚገኙ በመሆኑ ተናዛዡ የትኛውን የኑዛዜ አይነት ሊናዘዝ እና ሊፈጸም እንደሚችል ከህጉ እና ከበሽታው ባህሪ አንጻር እንመለከታለን።

1. በግልፅ የሚደረግ ኑዛዜ( Public will) ( የፍ/ብ/ህገ/ቁጥር 881-883)

በግልፅ የሚደረግ ኑዛዜ ተናዛዡ እየተናገረ ሌላ ሰው የሚፅፈው ወይም ተናዛዡ ራሱ የሚፅፈው የኑዛዜ አይነት ነው፡፡ ይህ ኑዛዜ በተናዛዡ ወይም በሌላ ሰው ከተፃፈ በኃላ ተናዛዡ እና ምስክሮች ባሉበት መነበብ አለበት፡፡ በግልፅ የሚደረግ ኑዛዜ ተቀባይነት እንዲኖረው ተናዛዡና ምስክሮች ባሉበት መነበቡ ብቻ በቂ አይደለም፡፡ ይልቁንም ይህ መስፈርት (formality) መሟላቱ በኑዛዜው ላይ መስፈር አለበት፡፡ ይኸውም በኑዛዜው ላይ "ይህ ኑዛዜ ተናዛዡ እና ምስከሮች ባሉበት ተነቧል" ተብሎ መገለጽ አለበት፡፡ በግልፅ በሚደረግ ኑዛዜ ላይ የምስክሮች ብዛት አራት ሲሆኑ አራቱም ምስክሮች ኑዛዜው ተነቦላቸው በኑዛዜው ላይ ፊርማቸውን ወዲያውኑ ማስፈር አለባቸው፡፡ በተጨማሪም በኑዛዜው ላይ ኑዛዜው የተደረገበት ቀን ማለትም ቀን፣ ወር፣ ዓመተ ምህረት መፃፍ አለበት፡፡

የምስክሮችን ብዛት በተመለከተ በግልፅ ለሚደረግ ኑዛዜ ከምስክሮቹ መካከል አንዱ ዳኛ ወይም ውል ለማዋዋል ሥልጣን የተሰጠው ሰው ሆኖ ኑዛዜውም የተደረገው ይህ ዳኛ ወይም ለማዋዋል ሥልጣን የተሰጠው ሰው ሥራቸውን በሚያካሄዱበት ክፍል ውስጥ የሆነ እንደሆነ ለኑዛዜው ዋጋ ማግኘት ሁለት ምስክሮች ብቻ በቂ ናቸው፡፡

በዚህ ኑዛዜ አይነት ተናዛዡም ሆነ ምስክሮች ባሉበት የሚፈጸም ሲሆን ነገር ግን ከበሽታው አስከፊነት አንጻር በሌላው ምስክር ሰው ላይ ሊተላለፍ የሚችል ገዳይ በመሆኑ ይህ ኑዛዜ ሊከናወን አይችልም።

2. በተናዛዡ ፅሁፍ የሚደረግ ኑዛዜ (የፍ/ብ/ህገ/ቁጥር 883-891)

በተናዛዡ ፅሁፍ የሚደርግ ኑዛዜ ሙሉ በሙሉ በተናዛዡ የሚፃፍ የኑዛዜ አይነት ነው፡፡ ይህን የኑዛዜ አይነት የሚያደርገው የተማረ ወይም ኑዛዜው የሚፃፍበትን ቋንቋ መፃፍና ማንበብ በሚችል ሰው ሲሆን የምስክሮችን መኖር የሚፈልግ አይደለም፡፡ በተናዛዡ ፅሁፍ የሚደረግ ኑዛዜ በተናዛዡ የእጅ ፅሁፍ ወይም በማሽን (በኮምፒዩተር) ሊፃፍ ይችላል፡፡ ተናዛዡ ኑዛዜውን በኮምፒዩተር የሚፅፈው ከሆነ በእያንዳንዱ ገፅ ላይ እራሱ ስለመፃፉ በእጅ ፅሁፉ ማመልከት አለበት፡፡ ይህም ኑዛዜውን ያደረገው ተናዛዡ እንደሆነ ለማረጋገጥ ይረዳል፡፡ ኑዛዜው በማሽንም ሆነ በእጅ ቢፃፍ ተናዛዡ በእያንዳንዱ ገፅ ላይ ቀን ፅፎ ፊርማውን ማስፈር ይኖርበታል፡፡ በተጨማሪም በኑዛዜ ሰነድ ላይ ተናዛዡ ይህ ሰነድ "ኑዛዜ" ነው በማለት በግልፅ መግለፅ አለበት፡፡ እነዚህ መስፈርቶች ካልተሟሉ ኑዛዜው ፈራሽ ነው፡፡ በተጨማሪ በተናዛዡ ፅህፈት የሚደረግ ኑዛዜ ኑዛዜው በተደረገ በሰባት(7) ዓመት ውስጥ ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው ሰው ወይም ፍርድ መዝገብ ቤት መቀመጥ አለበት።

ይህ የኑዛዜ አይነት በዚህ በማይበርግ በሸታ የተጠቃው ሰው ይህን ኑዛዜ ለማድረግ የሚያስችል ሁኔታ ወይም ጤንነት ወይም ብቃት ካለው በሌላ አነጋገር በጽኑ ህመም ውስጥ የማይገኝ ከሆነ የኑዛዜውን ወረቀት ሌላ ምስክር ሳያስፈልግ መጻፍ መፈረም የሚችል ሲሆን ነገር በወረቀቱ ንክኪ የማይተላለፍ ስለመሆኑ ከዚህ ጋር ተያይዞ ለተላላፊ አደጋ የማያጋልጥ ስለመሆኑ ሀኪሞች ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል።

3. የቃል ኑዛዜ (የፍ/ብ/ህገ/ቁጥር 892-893)

አንድ ሰው የቃል ኑዛዜ ማድረግ የሚችለው በተለይ በሚከተሉት ጉዳዮች ላይ ሲሆን እነዚህም ተናዛዡ እሞታለው ብሎ በማሰብ በጽኑ ህመም ውስጥ በሆነ ጊዜ ሲሆን የቃል ኑዛዜ ብቻ ህጉ የሚፈቅድለት ይሆናል። እነዚህም የቀብሩን ሥነ-ሥርዓት የሚመለከቱ እና እያንዳንዱ ውርስ ከአምስት መቶ የኢትዮጵያ ብር የማይበልጥ ብር እንዲሁም አካለ መጠን ላላደረሱ ልጆች ሞግዚት ወይም አስተዳዳሪ ለመሾም ሲሆን ሁለት ምስክሮች ባሉበት በቃል የሚደረግ ኑዛዜ ነው።

ይህን ስንመለከት የቀብር ስነስረአት ኑዛዜን በተመለከተ ቢናዘዝም እርሱ ባለው መሠረት ተፈጻሚ አይሆንም ለዚህም ምክንያቱ በማይበርግ ቫይረስ ተይዞ የሞተ ሰው እሬሳው ለቤተሰብ ስለማይሰጥ ነው። ሌላው ከአምስት መቶ ብር የማይበልጥ ለእያንዳንዱ ወራሽ እንዲወርስ ወይም
ለልጆች አስተዳዳሪ ሞግዚት ለመሾም የሚደረግ ኑዛዜ በተመለከተ ግን በኤሌክትሮኒስ ዘዴ በቪዲዮ ኮንፍረንስ ሁለት ምስክሮች ጋር በቪዲዮ ኮንፍረንስ እንዲገናኙ በማድረግ ተግባራዊ ለማድረግ የሚቀል ሲሆን ነገር ግን ይህ የቃል ኑዛዜ ከተደረገ እስከ ሶስት ወር ጊዜ ውስጥ ተናዛዡ ካልሞተ የቃል ኑዛዜው ተፈጻሚነቱ ይቀራል።

4. ማጠቃለያ

በእንደዚህ አይነት አስፈሪ እና ተላላፊ የሆኑ በሽታዎች በሚያጋጥሙ ጊዜ መደበኛ የህግ እንቅስቃሴዎችን ለማከናወን አስቸጋሪ ነው። ከዚህ አንጻር ኑዛዜዎችን በተለይም በተራ ቁጥር አንድ ላይ የተቀመጠውን የኑዛዜ አይነት ለማድረግ የተናዛዡን እና የምስክሮችን በአካል በአንድ ቦታ መገኘት መፈረም የሚጠይቅ በመሆኑ ፍጹም የማይቻል ነው። ሁለተኛው የኑዛዜ አይነት በቫይረሱ የተያዘው ሰው በጽኑ ህመም ውስጥ ካልሆነ የሚያደርገው ሲሆን ከሆነ ግን የሚፈቀድለት የቃል ኑዛዜ ብቻ ነው። በጽኑ ህመም ውስጥ ካልሆነ ግን ራሱ ተናዛዡ ብቻ የሚጽፈውና የሚፈርመው በመሆኑ ሊተላለፍ የሚችልበትን ሁኔታ ሌላ ከሌለ በቀር በጤና ባለሙያዎች ሲረጋገጥ ሊፈጸም የሚችል ነው። የቃል ኑዛዜን በተመለከተ ቀብርን አስመልክቶ የሚደረግ ኑዛዜ ተፈጻሚ አይሆንም ለዚህም ምክንያቱ ሲሞት እሬሳው ለቤተሰብ የማይሰጥ በመሆኑ ነው።

ይሁን እንጂ የአምስት መቶ ብር ውርስ እና የልጆች ሞግዚት ወይም አስተዳዳሪ አስመልክቶ ሁለት ምስክሮችን ፊርማ የማይጠይቅ በመሆኑ በቪዲዮ ኮንፍረስ ወይም በርቀት ምስክሮቹ በመሆን የጤና ባለሙያዎች ወይም ጤና ሚኒስተር ከበሽታው ተላላፊነት አንጻር ይህን ለማድረግ ካረጋገጡ ሊፈጸም የሚችል ነው።
https://www.facebook.com

28/07/2025
27/07/2025
11/10/2024

Address

Jemo Mikael
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when NAFMA Coffee posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category