Nigus Kitfo

Nigus Kitfo Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Nigus Kitfo, Restaurant, Wollo Sefer old Ibex Hotel, Addis Ababa.

12/03/2020
15/01/2020

የራስ ገዝ የሀገርዎን ይግዙ ንቅናቄ ምክንያተ ምስረታዉ የኢትዮጵያውያን የሀገርን ምርት የመግዛት እና የመጠቀም ባህልን ማነቃቃት እና ማጎልበት ነዉ፡፡
የራስ ገዝ እንቅስቃሴ ይዞ የተነሳውን አላማ ከግብ ለማድረስ በየዘርፉ ልዩ ልዩ እንቅስቃሴዎችን ያደርጋል፤ ከነዚህም እንቅስቃሴዎች አንዱ ለህዝቡ ተደራሽ የሆኑ የመገበያያ መድረኮችን ማዘጋጀት ነዉ።
የዚሁ እንቅስቃሴ አንዱ ዘርፍ ከጥር 9 2012 ዓ.ም የሚጀምረዉ የቅዳሜ ሀገራዊ ፋሽን ገበያ ነዉ፤ ገበያው የኢትዮጵያ እና ሀገራዊ የሆኑ የፋሽን ድርጅቶችን አካቶ የሃገር አልባሳት፣ጫማዎች፣ቦርሳዎች፣ ጌጣጌጦች እና የተለያዩ መዋቢያዎችን ላይ ትኩረት አድርጎ የተዘጋጀ ቋሚ የቅዳሜ ሳምንታዊ ገበያ ነው። ይህ ገበያ በተለይ ስም (ብራንድ) ለማትረፍ ከሚሰሩ ከ50 በላይ የሆኑ ዲዛይነሮች፣ አምራቾች፣ ጦማሪዎች፣ አልባሾች እና ሌሎች የሀገር ፋሽን ተሳታፊዎችን ጋር ይጀመራል፡፡
በዚህ ሳምንታዊ የቅዳሜ ገበያ በየሰአቱ፣ በየፈረቃው ፣ የፋሽን ሾው እና ትንተና ይኖራል፤ በየአጋጣሚው ታዋቂ ሰዎች እና ሚዲያዎች ገበያውን እንዲጎበኙት ይደረጋል፤ ከደምበኞች አስተያየት ይሰበሰባል፣ አምራቾች የልምድ ልውውጥ ያደርጋሉ እና ወዘተ፡፡
እግረ መንገዱንም አዲስ አበባን የአፍሪካ የፋሽን መዳረሻ ለማድረግ፣ ሀገሪቱ በቱሪስቶች የምትጎበኝበትን አንድ ተጨማሪ ምክንያት ለመሆን፣ ሀገራዊ የሆኑ ልብሶቻችን ከባዕላት እና ከልዩ ልዩ ፕሮግራሞች በዘለለ በየትኛውም ጊዜ ላይ እንድንገዛ እና እንድንጠቀም ለማላመድ፣ አምራቾችም ከመታዘዝ አልፈዉ አምርተው መሸጥ እንዲችሉ ለማገዘ፣ ለውጪ ሀገር ገበያ ብቁ እና ተወዳዳሪ የሆኑ ምርቶችን እንዲያመርቱ ለማስቻል እንዲሁም ስለጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ለምሳሌ የፋሽን ዲዛይነሮችን ፣ ጦማሪያን፣ የፋሽን ት/ቤቶች ፣ እና የፋሽን ሀያሲያን እርስ በርስ ለማስተሳሰር ይረዳል።
አንግዲህ እርሶዎ እና የተከበረ ድርጅትዎ የዚህ የሀገርዎን ይግዙ ንቅናቄ አጋር እንዲሆኑ አልፎም በዚህ ሳምንታዊ ዝግጅት ላይ እርስዎ፣ የስራ ባልደረቦችዎ፣ ወዳጆችዎ እና ቤተሰብዎ እንዲገኙ፣ እንዲጎበኙ፣ እንዲገበያዩ በትህትና እንጋብዛለን፡፡
ስፍራ፡ ቦሌ ወሎ ሰፈር፣ ንጉስ ባህላዊ ሆቴል (የቀድሞ አይቤክስ ሆቴል) ላይ፡፡ ስልክ፡ 0947 16 16 16

Address

Wollo Sefer Old Ibex Hotel
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Nigus Kitfo posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category