Serke

Serke Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Serke, Pub, Addis Ababa.

✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜንን አሜንን አሜንን ።                       ቃና ዘገሊላ  ጥር 12 ‹‹ቃና ዘገሊላ›› ምንድ...
20/01/2023

✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜንን አሜንን አሜንን ።

ቃና ዘገሊላ

ጥር 12 ‹‹ቃና ዘገሊላ›› ምንድነው?
➡ቃና ዘገሊላ በቀጥታ ትርጉም የገሊላዋ ቃና ማለት ነው፡፡ እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን አስተምህሮ በጥምቀት በዓል ማግስት(ጥር 12) ቀን የቃና ዘገሊላ በዓል ይከበራል፡፡

ይህ በዓል ከጌታ ጥምቀት በዓል ጋር ተያይዞ በድምቀት የሚከበር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ዳራ ያለው በዓል ነው፡፡ በዓሉ ቃና ዘገሊላ የሚል ስያሜ ያገኘው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የገሊላ ሀገር ክፍል በምትሆን ቃና በተባለችው ቦታ በፈፀመው ተአምር መነሻነት ነው፡፡ የቃና ዘገሊላ ጥንተ ነገሩ ወይም ታሪኩ የተፈፀመው የካቲት 23 ቀን ነው፡፡

ነገር ግን አባቶቻችን የውኃን በዓል ከውኃ በዓል ጋር ለማክበር ብለው የየካቲቱን በዓል ወደ ጥር 12 አምጥተውታል፡፡ ይህም ውኃ ወደ ወይን የተለወጠበትን በዓል ከጌታ ጥምቀት በዓል ጋር ለማስተሣሠር ለማስኬድ ነው፡፡ በመሆኑም የቃና ዘገሊላ በዓል ጥር 12 ቀን ይከበራል፡፡
በቃና ዘገሊላ ምን ተፈፀመ? ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የገሊላ ክፍል በምትሆን በቃና በተደረገ ሠርግ ላይ ከእናቱ ከድንግል ማርያም ጋር ተገኝቶ ነበር፡፡ ‹‹ወሀለወት ህየ እሙ ለእግዚእ ኢየሱስ›› ‹‹የጌታ የኢየሱስ እናትም በዚያ ነበረች›› እንዳለ ቅዱስ ዮሐንስ በወንጌሉ (ዮሐ 2÷1) እመቤታችን ለሠርገኞቹ ዘመድ ነበረችና ከልጇ ከወዳጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ በሰርጉ ላይ ታድማ ነበር፡፡

እናትን ጠርቶ ልጅን መተው ሥርዓት ስላልሆነ፤ በተጨማሪ ደግሞ ደቀ መዛሙርቱ ከጌታ ጋር በሰርጉ ታድመዋል፡፡ ይህም መምህርን ጠርቶ ደቀ መዛሙርቱን መተው ሥርዓት ስላልሆነ (ተገቢ ስላልሆነ) ነው፡፡ የሠርጉ ሥነ-ሥርዓት በሠመረ ባማረ ሁኔታ እየተከናወነ ሳለ ድንገት የወይን ጠጅ አለቀ፡፡

አስተናባሪዎቹ በጭንቀት ባሕር ሰጥመው ምን እንደሚያደርጉ ግራ በገባቸው በጠበባቸው ጊዜ የችግር ጊዜ ደራሽ የኃዘን ጊዜ አፅናኝ የሆነችው የአምላክ እናት ድንግል ማርያም ቅዱስ ገብርኤል እንደተናገረ በፀጋ የተሞላች ናትና (ሉቃ 1÷28) ማንም ሳይነግራት የልቦናቸውን ጭንቀት አይታ፣ ጎዶሎአቸውን ተመልክታ ወደ ልጃ_ ወደ ወዳጃ_ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘወር ብላ ‹‹ወይንኬ አልቦሙ›› ‹‹ወይን ጠጅ እኮ አልቆባቸዋል›› አለችው፡፡

እርሱም መልሶ ‹‹አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ?›› ‹‹ጊዜዬ ገና አልደረሰም›› አላት፡፡ እመቤታችንም ለአገልጋዮቹ ‹‹የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ›› አለቻቸው፡፡ ጌታም በቦታው የነበሩ ስድስት ጋኖች ውኃ ሞልተው እንዲያመጡ አዘዛቸው፡፡ ውኃውንም ወደ ወይን ለውጦ ለሊቀ ምርፋቅ (ለአሳዳሪው) እንዲሠጡት አዘዘ፡፡ አሳዳሪውም ወደ ወይን የተለወጠውን ውኃ በቀመሰ ጊዜ አደነቀ፡፡ ከወዴት እንደመጣ ስላላወቀ ሙሽራውን ‹‹ሰው ሁሉ አስቀድሞ መልካሙን የወይን ጠጅ ያቀርባል ከሰከሩም በኋላ መናኛውን ያቀርባል አንተ ግን መልካሙን እስከ አሁን አቆይተሃል›› አለው፡፡

ወይኑም በሰው እጅ ያይደለ በሠማያዊው አባት የተዘጋጀ ስለነበር ጣፋጭ እና ልብን የሚያስደስት ነበር፡፡ ‹‹አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ?›› ይህንን የጌታችንን ንግግር ብዙዎች በዘመናችን ሲሣሣቱበት ይታያል ፡፡ ክብር ይግባውና አምላካችን ይህንን የተናገረው እናቱን ሊያቃልል ሽቶ አይደለም፡፡ ስለሆነም ከመጽሐፍ ቅዱስ አንፃር ይህን አረፍተ ነገር መመልከቱ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ በተናጠል ስንመለከት ‹‹አንቺ ሴት›› ሴት የሚል ቃል የፆታ መጠሪያ ነውና በፆታዋ አክብሮ ሲጠራት ነው፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ሔዋን ከአዳም በተፈጠረች ጊዜ አዳም እንዲህ ሲል ተናግሮ ነበር ‹‹ይህች አጥንት ከአጥንቴ ናት ሥጋም ከሥጋዬ ናት እርስዋ ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል›› (ዘፍ 2÷23) በመሆኑም ጌታ አንቺ ሴት ማለቱ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍስዋ ነፍስ መንሣቱን ለማጠየቅ ነው፡፡ ‹‹ከአንቺ ጋር ምን አለኝ?›› የሚለውን ዐረፍተ ነገር የንቀት ስለመሰለን ብቻ ‘ የዳቦ መልክ የያዘ ድንጋይ፤ ዳቦ ነው እንደማይባል’ የንቀት ንግግር ነው ልንል አይገባም፡፡

ጌታም እንዲህ ሲል ውኃውን ወይን አድርግላቸው ብትይኝ አላደርግም እልሽ ዘንድ ከአንቺ ጋር ምን ፀብ አለኝ ማለቱ ነው፡፡ ይህ ንግግር በመጽሐፍ ቅዱስ በብዙ ቦታ ተጽፎ እንደሚገኘው በዕብራውያን ዘንድ የተለመደ የአነጋገር ዘይቤ ነው፡፡ለአብነት ይሆን ዘንድ ጥቂት ጥቅሶችን ከመጽሐፍ ቅዱስ እንመልከት፡- የሰራፕታዋ ሴት በ 1ነገ 17÷18 ላይ እንደምናገኘው ልጇ በሞተባት ጊዜ ኤልያስን በሐዘን በለቅሶ እንዲህ ብላ ነበር ‹‹የእግዚአብሔር ሰው ሆይ ከአንተ ጋር ምን አለኝ?›› ትወልጃለሽ ብለህ የወለድኩት ልጅ ምን በድዬህ ምንስ አስከፍቼህ ሞተብኝ? ስትል ነው እንጂ አባባሏ የንቀት ወይም የማቃለል አይደለም፡፡

በጌርጌሴኖን አንድ አጋንንት ያደረበት ሰው ወደ ጌታችን ቀርቦ ‹‹የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ከአንተ ጋር ምን አለኝ?›› አለው፡፡ እውነት ይህ ቃል የንቀት ይመስላልን? የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ብሎ አምላክነቱን እየመሰከረ ሊያቃልለው ይችላልን? ደግሞስ ላለመጥፋት ፍፁም የሚፈልግ ሰው ሊያድነው ሥልጣን ያለውን ሊንቅ ይችላልን? አይችልም፡፡ ይህ ቃል የሚያመለክተው ምን አጠፋሁ ስለምን ልታጠፋኝ ወደድክ በማለት መፍራት መራዱን ነው፡፡ (ሉቃ 8÷28-29) ስለሆነም ‹‹አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ?›› የሚለው የንቀት አለመሆኑን ከሁለቱ ጥቅሶች መረዳት እንችላለን፡፡ እመቤታችን እና ጌታ በንግግር አልተቃረኑም ንግግራቸው የፍቅር ነበር፡፡

ንግግራቸው የመግባባት ስለነበር ነው ‹‹አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ?›› ካላት በኋላ ዘወር ብላ አገልጋዮቹን የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ ያለችው፡፡ ‹‹ጊዜዬ አልደረሰም›› ጌታ ይህን ቃል የተናገረው ስለ ብዙ ምክንያቶች ነው፡፡ ጊዜዬ አልደረሰም ማለቱ፡- እግዚአብሔር ነገሮችን የሚያከናውንበት የራሱ ጊዜ አለው፡፡ በመሆኑም ይህን ተአምር የምፈፅምበት ጊዜዬ አልደረሰም ሲል ነው፡፡ ጋኖቹ ውስጥ የቀረ ወይን ስለነበረ ባለው ላይ አበርክቶ እንጂ ውኃውን ወደ ወይን አልለወጠውም እንዳይሉ ወይኑ ከጋኑ ተንጠፍጥፎ እስኪያልቅ ድረስ ጊዜዬ አልደረሰም አለ፡፡

ይሁዳ ከሠርግ ቤት ወጣ ብሎ ነበርና ወደ ሠርግ ቤቱ እሰኪመለስ ጊዜዬ አልደረሰም አለ፡፡ ይሁዳ በቃና የገለጠውን ምስጢር ለእኔ ስላላሣየኝ ተከፍቼበት ከተአምራቱ ቢያጎድለኝ በሞቱ ገባሁበት፤ ሸጥኩት እንዳይል ምክንያት ለማሳጣት እንዲህ አድርጓል፡፡ እውነተኛ የሕይወት ወይን የሆነውን ደሜን የምሠጥበት ጊዜ ገና ነው ሲል፡፡ የድንግል ማርያም አማላጅነት በገሊላ ቃና ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በሠርግ ቤት ሣለ የወይኑን ማለቅ የማይመለከት ሆኖ አይደለም፡፡ ነገር ግን የእናቱን የድንግል ማርያምን አማላጅነት ሊገልጥ ስለወይኑ ማለቅ እስክትነግረው ድረስ አንዳች ነገር አላደረገም፡፡

ኋላ ግን የጭንቀት አማላጅ ድንግል ማርያም ስለ ወይኑ አሰበች ልጇ ወዳጇን ለመነች፡፡ እርሱም የእናቱን ልመና ተቀብሎ ተአምራቱን ፈፀመ፡፡ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሣይነግሯት በልብ ያለውን የምታውቅ የምትመረምር እናት ናትና የሠርጉ አስተናባሪዎች ይሄ ጎደለ ሣይሏት የልቦናቸውን ሐዘን ተመልክታ ከልጇ ከወዳጇ አማልዳ የጎደላቸውን ሞልታለች፡፡ ያስጨነቃቸውንም አርቃለች፡፡ በችግራቸው ደርሳላቸዋለች፡፡ ታዲያ ሳይነግሯት የልቡናን አይታ ከማለደች ስሟን ጠርተው ለሚለምኗትም እንዴት አብልጣ አታማልድ? ከእናታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ረድኤቷን በረከቷን ያሳድርብን አሜን አሜን አሜን ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር።

ወስበሐተ ለእግዚአብሔር
ወለወላዱቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር ይቆየን
አሜንን. አሜንን. አሜንን
አሜንን. አሜንን. አሜንን
አሜንን. አሜንን. አሜንን

ጥር፯ ቀን እንኳን ለአጋእዝተ ዓለም ቅድስት ስላሴ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን የተዋህዶ ልጆች💓🙏በባቢሎን በሰናዖር የተፈጸመውን ተአምር 🖊•••ሥላሴ የሚለው ቃል‹‹ሠለሰ›...
15/01/2023

ጥር፯ ቀን እንኳን ለአጋእዝተ ዓለም ቅድስት ስላሴ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን የተዋህዶ ልጆች💓🙏

በባቢሎን በሰናዖር የተፈጸመውን ተአምር
🖊•••ሥላሴ የሚለው ቃል‹‹ሠለሰ››ሦስት አደረገ ከሚለው የግዕዝ ሥርወ ቃል የተገኝ ሲሆን ይህም ሦስትነት ማለት ነው፡፡ምሥጢረ ሥላሴ ብለን ስለነገረ ሃይማኖት ስንናነገር ግን አንድም ሦስትም ተብሎ ይተረጎማል፡፡ በዚህም መሠረት እግዚአብሔርን አንድም ሦስትም ብለን ማመናችንን የምንገልፅበት የሃይማኖት ዶግማ ነው፡፡እንደሚታወቀው የሥላሴ አንድነት ስንል በባህርይ በህልውና በፈቃድ….አንድ አምላክ ማለታችን ሲሆን ሦስትነት ስንል ደግሞ በስም’በአካል’በግብር ነው፡፡የሥላሴ አንድነት እና ሦስትነትን ከሚገልጹ ማስረጃዎች ለአብነት፡-

🖊‹‹እግዚአብሔርም አለ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌያችን እንፍጠር››ዘፍ.1.26 ‹‹እግዚአብሔርም አለ ብሎ አንድነቱን‹‹ሰውን በመልካችን እንፍጠር››ብሎ ሦስትነትን ይገልጻል፡፡እንደ ዚሁም እነሆ አዳም መልካምንና ክፉን ለማወቅ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ ዘፍ.3.22 ይህ ኃይለ ቃል‹‹ከእኛ›› የሚለውና‹እንደ አንዱ›የሚለው የሦስትነት ምሥጢር የሚጠቁም መሆኑን ሊቃውንት ያስረዳሉ፡፡ በዘመነ ኦሪት የሥላሴ ምሥጢር ከተገለጠበት አንዱ ለአብርሃም በመምሬ አድባር ዛፍ ሥር ነው፡፡ዘፍ.18፡1-15 በዚህ ምዕራፍ እግዚአብሔር ለአብርሃም እንደ ተገለጠለት ወዲያውም ሦስት ሰዎች እንደ ተመለከተ አብርሃምም ሊቀበላቸው ሲጠጋ በመስገድ ‹‹አቤቱ በፊትህ ሞገስን አግኝቼ እንደሆነ›› ብሎ አንድነቱን መግለጹን አያይዞም ደግሞ“ጥቂት ውሃ ይምጣላችሁ” ብሎ በአካል ሦስት መሆናቸውን ተናገረ፡፡ በአጠቃላይ በምዕራፉ የአንድነት እና የሦስትነት ነገር እናስተውልበታለን፡፡
ነቢየ ልዑል ኢሳይያስ ‹‹ቅዱስ’ቅዱስ’ ቅዱስ እግዚአብሔር…›› ብለው ቅዱሳን መላእክት እንደ ሚያመሰግኑ መመሥከሩ ከሦስት ሳያሳንስ’ እና ሳያስበልጥ መጠቆሙ
የሥላሴን ሦስትነት የሚያሰረዳ ነው፡፡

🖊•••ኢሳ.6.1-3 የሥላሴ ሦስትነት ስንል-
በስም፡-አብ፤ወልድ፤መንፈስ ቅዱስ ማለታችን ነው፡፡‹‹ወእንዘ ታጠምቅዎሙ በሉ በስመአብ፤ወወልድ፤ ወመንፈስ ቅድስ›› እንዲል ማቴ.28.19 በአካል፡-ለአብ ፍጹም ገጽ ፍጹም አካል አለው ለወልድ ፍጹም ገጽ ፍጹም አካል አለው ለመንፈስ ቅድስ ፍጹም ገጽ ፍጹም አካል አለው ብለን ማመናችንን ነው ይህም የማይወሰን የማይለካ ረቂቅ አካልን ነው፡፡መዝ.33.15 መዝ.118.73 ዘፍ.18

🖊•••በግብር ሦስትነት ስንል፡-የአብ ግብሩ መውለድ፤ማሥረጽ፤ የወልድ ግብሩ መወለድ የመንፈስ ቅዱስ ግብሩ መሥረጽ ወይም አብ አባት፣ወልድ ልጅ ፣መንፈስቅዱስ ሠራፂ ማለታችን ነው፡፡ኢሳ.48.12 መዝ.118.16 ዮሐ 16 ÷7-19በቅዱስ ወንጌል በዮርዳኖስ እና በደብረ ታቦር የሥላሴ ምሥጢር ገሀድ ለመሆኑ ማስረጃ ሆኖ ይጠቀሳል፡፡ማቴ. 3.16 ማቴ.17 መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ስብከቱ ‹‹አነ ወአብ አሐዱ ንህነ››እኔና አብ አንድ ነን ማለቱ እና ‹‹እኔን ያየ አብን አየ››ብሎ ማስተማሩ ነገረ ሥላሴን ያስረዳል ዮሐ.10.30 (14÷11) በይበልጥ አብ ወላዲ፣ ወልድ ተወላዲ መንፈስ ቅዱስ ሠራጺ በማለታችን መበላለጥ እንደሌላቸው በሥልጣን በፈቃድ አንድ መሆንን ያስገነዝበናል፡፡ለዚህም ነው!

🖊•••አባ ሕርያቆስ‹‹ኢይልህቅ አብ እምወልድ ወልድኒ ኢይንዕስ እመንፈስ ቅዱስ ወመንፈስ ቅዱስኒ ኢይንዕስ እምወልድ ወወለድኒ አይንዕስ እምአቡሁ››በማለት እንደማይበላለጡ አስረድቶናል፡፡እንደዚሁም ሦስት አማልክት እያልን ሳይሆን አንድ አምላክ ማለታችን እንደሆነም እሙን
ነው፡፡‹‹ወመለኮትሰ አብ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ እንዳለው አባ ሕርያቆስ (ቅዳሴማርያም)በምሳሌም ለመረዳት ፀሐይ ከኮብ፡ብርሃን፡ሙቀት፡እሳትም ነበልባል፡ፍሕም፡ሙቀት፡ሲኖራቸው ሦስት ፀሐይ ሦስት እሳት አይባሉም አንድ ፀሐይ አንድ እሳት እንጂ እንደዚሁ ሥላሴ በስም በአካል በግብር ሦስት ቢባሉም ቅሉ አንድ አምላክ እንጂ ሦስት አማልክት አይባሉም 2ኛ ቆሮ.13.14 ኤፌ. 4÷4

🖊•••በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/ምሥጢረ ሥላሴ የሃይማኖት ዶግማ እና የሥርዓተ አምልኮ ሁሉ መግለጫችን ነው፡፡ጸሎታችን፣ጥምቀታችን፣ ቡራኬያችን….ሁሉ በስመ ሥላሴ ነው፡፡
ይህም እንዳለ ሆኖ ነገረ ሥላሴን በበዓል ለመመስከር እና የቸርነቱ፣የምህረቱ ተካፋይ ለመሆን በዓለ ንግሥም ይከናወናል፡፡ በይበልጥም ሐምሌ 7 ቀን ለአብርሃም በድንኳን ደጃፍ መገለጡን እና ጥር 7 በባቢሎን በሰናዖር የተፈጸመውን ተአምር በማሰብ እናከብራለን፡፡ ዘፍ.18 ዘፍ.11.1-9

🖊•••በመጽሐፍ ቅዱስ እና በቅዱሳት አዋልድ መጻሕፍት እንደተመዘገበው ከጥፋት ውሃ በኋላ የኖኅ ልጆች ወልደው ተዋልደው ብዙዎች ሆኑ፡፡በባቢሎን የነበሩት በሰናዖር ሰፊ ሜዳ አግኝተው ‹ሳንሞት ስም ማስጠሪያ ግንብ እንገንባ›ብለው መክረው ታላቅ ግንብ ገነቡ፡፡አለቃቸው ናምሩድ ይባላል‹‹ሞትን የሚያመጡብን ሥላሴ ናቸውና እነርሱን ወግተን ሞትን እናርቅ››አላቸው ከዚያም ሆነው ጦር እየሰበቁ ይወረውሩ ጀመር ሰይጣን ከደመና በምትሀት ደም እየቀባ ይልክላቸዋል እነርሱም ደሙን እያዩ‹‹አሁን አብን ወጋነው አሁን ወልድን ወጋነው…››ይሉ ጀመር ቅድስት ሥላሴ ምንም እንኳ ምህረታቸው የበዛ ቢሆንም በሕዝቡ ላይ ዲያብሎስ ስለሠለጠነባቸው እና ለሌሎች ከሀድያን ትምህርት ይሆን ዘንድ‹‹ንዑ ንረድ ወንክዐው ነገሮሙ››በማለት ቋንቋቸውን ለያዩባቸው የማይግባቡ፣የማይደማመጡ…ሆነው ተበታትነዋል፡፡ባለማስተዋል የሠሩትንም ሕንፃ ዓመጻ ነፋስ ጠራርጎ አጥፍቶታል፡፡ይህን ያደረጉ ሥላሴ በመሆናቸው በዓሉ ጥር 7 ይከበራል፡፡

🖊•••በአጠቃላይ ሥልጣን ሁሉ የእግዚአብሔር መሆኑን እና በራስ ደካማ አመለካከት እንዳተበይ ያስረዳሉ፡መጠራጠር እንደሚጎዳ እንደዚሁም በጽኑ እምነት በመኖር እና በሥላሴ ስም የተጠመቅን ልጅነታችንን በኃጢአት ሳናሳድፍ በንስሐ ታጥበን እና በምግባር ጸንተን መጠበቅ እንደሚገባ የበዓሉ መልእክት ያስገነዝበናል፡፡የታማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ እንደሚል፡፡ኤፌ.4÷30🙏

03/12/2022

Watch, follow, and discover more trending content.

በጥቅምት እኩሌታ አንድ ኩታ
24/10/2020

በጥቅምት እኩሌታ አንድ ኩታ

ተከብረሽ የኖርሽው በአባቶቻችን ደም እናት ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይውደም
03/10/2020

ተከብረሽ የኖርሽው በአባቶቻችን ደም እናት ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይውደም

Address

Addis Ababa
TOMAS

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Serke posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category