BBETE

BBETE I would like fast food & Restorant

04/06/2026

ይህ ወንድማችን ይባላል!የተወለደው አዳማ ነው!ከጠፋ 2ዓመት አልፎታል፣ለመጨረሻ ጊዜ ቁስቋም ማርያም ታይቷል ተብሏል! ቤተሰቦቹ በፍለጋ እየተንከራተቱ ነው! እባካችሁን #ሼር በማድረግ አፋልጉን🙏
"ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም"

0910199901
0910199902

04/06/2026

የጠፋ ልጅ መረጃ - ሼር በማድረግ ይተባበሩ!

ከታች በፎቶ የምታዩት ህፃን በአሁኑ ሰዓት ከመንገድ ተገኝቶ ቤተሰቦቹን እየፈለገ ይገኛል። ስሙን ሲጠየቅ "ማሂር" እንደሚባልና የአባቱን ስም "አባ" እያለ ይናገራል።

ህፃኑ በአሁኑ ሰዓት የሚገኘው ዱና አካባቢ ወደ ካባ በሚወስደው ዋናው መንገድ፣ ስቴዲየሙ መጨረሻ አካባቢ ቀረብ ብሎ፣ ከሚገኙት ወፍጮ ቤቶች ፊት-ለፊት ካሉት ቤቶች በአንዱ በጎ አድራጊ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ ነው።

የህፃኑ ቤተሰቦች ወይም የምታውቁት ሰዎች ካላችሁ ከታች በተቀመጡት የሞባይል ስልክ ቁጥሮች በአስቸኳይ ደውላችሁ ማግኘት ትችላላችሁ።

0910871518 — አድሩስ ሰለሞን
0910300444 — ሸምሴ አህመድ

ይህ መረጃ ለቤተሰቦቹ በፍጥነት እንዲደርስና ህፃኑ ከቤተሰቡ ጋር እንዲቀላቀል ሁላችሁም ሼር (Share) በማድረግ ተባበሩን። እግዚአብሔር ያክብርልን።

🙏🙏🙏

04/06/2026

Share Share በውሥጥ መስመር በርካቶቻችሁ የቅዳሜው በ AFTV አድሚኖች ሊዘጋጅ ፕሮግራም የተያዘው በቅርቡ አሩሲ ውሥጥ በተፈጸመው ንጹሃኖች ላይ በደረሰው ሞት ይህ ፕሮግራም እንዳይደረግ ከታቸለ ወደ ሌላ ግዜ እንዲዘዋዋር ይደረግ ይህን ፖሥት ሼር አርጉት ....

ስልጡኑ የአዲስ አበባ ሕዝብ ሁሉን በጊዜው: በቦታው እና በልኩ በማድረግ የሚታወቅ ነው።

የአዲስ አበባ ልጅ ጎረቤቱ ሀዘን ሲመጣ ሰርጉን እንኳን የሚያሸጋግር ነው። ቴሌቭዥን ከፍቶ ዜና ለመስማት እንኳን የሚሳቀቅ ነው። ዘር እና ሃይማኖት ሳይመርጥ የሚቀብር እና የሚያስተዛዝን ነው።

የአርሰናል ደጋፊ የሆኑ ወጣቶች በአዲስ አበባ ለግንቦት 29 የሙዚቃ ድግስ ቀድመው አዘጋጅተዋል። ነገር ግን በዚህ ሳምንት ከ40 በላይ ወገኖቻችን ተገ* ድለው: በመቶዎች የሚቆጠሩ ተፈናቅለው እና ብዙዎች ቤት ንብረታቸው ወድሞ እኛ ልንደሰት አንችልም። የመፈናቀልን ሕመም ለአዲስ አበባ ልጅ ማስታወስ አያስፈልግም።

ይህንን ድግስ በዚህ ወቅት ማድረግ ግ* ድያ እና ጭፍ* ጨፋን ማቅለል እና ማለማመድም ይሆናል። የስፖርትም ጌጡ አብሮነት ነው።

ይህ ሳምንት ወገኖቻችንን የምናስብበት እና ይህ ጭፍጨፋ ደግሞ እንዳይከሰት ምን ማድረግ እንዳለብን የምንመክርበት ብቻ ነው።

#ድግሱንሰርዙት
#አልዘነጋነውም #አዲስአበባ #ኢትዮጵያ

04/06/2026

በከተማችን አዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ የተቀረጸና በአሁኑ ወቅት በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ እየተዘዋወረ የመጣ አንድ አጭር ቪዲዮ የብዙዎችን ትኩረት ከመሳቡም በላይ የምግብ ንጽሕና አጠባበቅን አስመልክቶ ትልቅ ውይይት አስነስቷል። ይህ በሰፊው መነጋገሪያ የሆነው ምስል የሁላችንም የዕለት ተዕለት የምግብ ዋልታ በሆነው እንጀራ አያያዝና አቅርቦት ላይ የተጋረጠውን እጅግ አሳሳቢ ድክመት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ሆኖ ተገኝቷል።
በቪዲዮው ላይ በግልጽ እንደሚታየው፣ እንጀራ የሚያከፋፍል አንድ ወጣት በጎዳና ዳር በቆመች ሲልቨር የቪትዝ መኪና ፊት ለፊት (ቦኔት) ላይ በርካታ እንጀራዎችን ዘርግቶታል። በድርጊቱ ላይ ምንም ዓይነት ንጣፍ፣ ፌስታል ወይም መከላከያ ወረቀት ያልተጠቀመ ሲሆን፣ እንጀራዎቹ በቀጥታ ከመኪናው አቧራማ ብረት ጋር እየተነካኩ ሲታጠፉና አንዱ በሌላው ላይ ተደራርበው ለሽያጭና ለሥርጭት ሲዘጋጁ ይታያል። ወጣቱ መኪናውን እንደ መደበኛ የእንጀራ ማጠፊያ ጠረጴዛ በመጠቀም ሥራውን ያለምንም ስጋት ሲያከናውን መመልከት የብዙዎችን አይን የያዘና ያስገረመ ክስተት ሆኗል።
ይህ ድርጊት በማኅበረሰቡ ዘንድ ከፍተኛ ቁጣንና ድንጋጤን የፈጠረው ያለ ምክንያት አይደለም። መኪናው የቆመው በሕዝብና በተሽከርካሪ ግርግር መሃል በመሆኑ፣ በላዩ ላይ የሚረግፈው የአየር ላይ ጭስና አቧራ በቀጥታ ወደ ምግቡ ውስጥ ይገባል። ከዚህም በላይ እንጀራ እንደ ሌሎቹ አትክልቶች ታጥቦ ወይም እንደ ሥጋ ተቀቅሎ የሚበላ ባለመሆኑ፣ በዚህ መልኩ ለቆሻሻ ተጋልጦ መዘጋጀቱ ለተለያዩ የሆድ ዕቃና ለከፋ ተላላፊ በሽታዎች በቀጥታ የሚያጋልጥ በመሆኑ ጉዳዩን እጅግ አደገኛ ያደርገዋል። አብዛኛው የከተማው ነዋሪ እንጀራ ከሱቅ ሲገዛ ንጹሕ በሆነ ቦታ ተዘጋጅቶ የመጣ ቢመስለውም፣ ይህ ቪዲዮ ግን ከጀርባ ያለውን አስደንጋጭ እውነታ ይፋ አድርጓል።
ኢትዮ ሊድ በገለልተኝነትና በነጻ ጋዜጠኝነት ሚናው እንደሚታዘበው፣ ይህ ክስተት በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ለቀልድና ለፈገግታ የሚጋበዝ ቢመስልም ከበስተጀርባው ግን በከተማችን ላይ ሥር የሰደደ የምግብ ንጽሕና ቁጥጥር ክፍተት እንዳለ ያሳያል። እኛ የምንመገበው ምግብ የትና እንዴት እንደሚጓጓዝ ጥብቅ ክትትል ሊደረግበት የሚገባ ሲሆን፣ የሚመለከታቸው የጤና እና የቁጥጥር ባለሥልጣናት መሰል የጎዳና ላይ ፍጹም ኃላፊነት የጎደላቸውን አሠራሮች በጥብቅ ሊመረምሩና ሕጋዊ እርምጃ ሊወስዱ ይገባል። ከተገቢው ትርፍና ከሥራ መቅለል በላይ የሰው ልጅ ጤና እና ደኅንነት ሁልጊዜም ቀዳሚው ሊሆን ይገባል።

04/06/2026

ዛሬ ረፋድ ላይ በሆለታ የወልመራ ወረዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ውስጥ መላውን ማኅበረሰብ ያስደነገጠ እና እጅግ አሰቃቂ የሆነ ልብ የሚሰብር ድርጊት ተፈጽሟል። በአንድ የኮንትራት ወይም የቤተሰብ ክርክር ችሎት ላይ ጉዳዩን ሲከታተል የነበረ ተከሳሽ፣ በዕለቱ በችሎቱ ተገኝታ ውሳኔ ስታነብ የነበረችውን ዳኛ እና በሕግ ሲከራከራት የነበረችውን ሚስቱን በሽጉጥ ተኩሶ ሕይወታቸውን በአሰቃቂ ሁኔታ አጥፍቷል።
ከተአማኒ ምንጮች በደረሰን መረጃ መሠረት፣ በችሎቱ ላይ የግራ ቀኙን ክርክር መርምራ የመጨረሻውን የፍርድ ውሳኔ በንቃት ስታነብ የነበረችውና በምስሉ ላይ የምትታየው ወርቄ ፈካንሳ የተሰኘችው ወጣት ዳኛ፣ በባለጉዳዩ በድንገት በተተኮሰባት ጥይት በሥራ ገበታዋ ላይ እያለች ሕይወቷ አልፏል። ግለሰቡ ከዳኛዋ አንደበት የፍርድ ውሳኔውን እየሰማ በነበረበት በዚያው ቅጽበት፣ በእልህና በጭካኔ ተሞልቶ በድብቅ ይዞት በገባው ሽጉጥ መጀመሪያ የገዛ ሚስቱን፣ በመቀጠልም ፍትሕ ለማስፈን ስትደክም የነበረችውን ዳኛ በጥይት በመምታት የፍትሕ አደባባዩን በአንድ ጀምበር የደም ምድር አድርጎታል።
ይህ አሳዛኝ ክስተት በማኅበራዊ ሚዲያና በሕግ ባለሙያዎች ዘንድ ከፍተኛ ቁጣንና ድንጋጤን የቀሰቀሰ ሲሆን፣ “ሕግና ፍትሕ ይከበርባቸዋል፣ የሰላም መጠለያዎች ናቸው” ተብለው በሚታመኑ የፍርድ ቤት አደባባዮች ላይ ባለጉዳዮች ገዳይ የጦር መሣሪያ ይዘው መግባት መቻላቸው የፍርድ ቤቶቹን የጸጥታና የፈተሻ አጠባበቅ ትልቅ ክፍተት በግልጽ ያሳየ ሆኗል። የዜጎችና የሕግ አስከባሪዎች ደኅንነት ባልተጠበቀበት፣ የጦር መሣሪያ ይዞ ፍርድ ቤት በሚገባበትና የሰላማዊ ሰዎች ሕይወት በዋዛ በሚቀጠፍበት በዚህ ዘመን፣ በፍትሕ ሥርዓቱ ላይ የሚስተዋለው የደኅንነት ክፍተት በአስቸኳይ ሊፈተሽ ይገባል። ለተጎጂ ቤተሰቦችና ለፍትሕ አካላት በሙሉ መጽናናትን እንመኛለን።

01/06/2026

በአዲስ አበባ ከተማ ከ 3 ሺህ በላይ የሚሆኑ ቀባሪ የሌላቸው ዜጎች የቀብር ሥርዓት መፈጸሙ ተገለጸ።

👉 የ1 ሺህ 355ቱ ጾታቸው አለመታወቁን ገልፀዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ ብቻ አስከሬናቸውን የሚረከብ ፈላጊ ያጡ 3 ሺህ 236 ባይተዋር ሟቾች የቀብር ሥነ-ሥርዓት መፈጸሙን የከተማ አስተዳደሩ የሴቶች፣ ሕፃናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ለአሐዱ አስታውቋል።

የቀብር ሥነ-ሥርዓት ከተፈጸመላቸው ውስጥ 2 ሺህ 288ቱ ጨቅላ ሕፃናት መሆናቸውን የተናገሩት የቢሮው የዘላቂ ማረፊያ ቡድን መሪ አቶ ሰበታ ኡፍጋ ፤ የ1 ሺህ 355ቱ ጾታቸው አለመታወቁን ገልፀዋል።

በዘጠኝ ወራት ውስጥ የ748 አዋቂዎች አስከሬን የቀብር ስርዓት የተፈፀመ ሲሆን 667ቱ ወንዶች እና 81ዱ ሴቶች መሆናቸውን ጠቁመዋል።

ቢሮው በአሁኑ ወቅት ይህንን የባይተዋር ሟቾች የቀብር አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው በአዲስ ከተማ፣ በጉለሌ፣ በአራዳ፣ በየካ፣ በቃሊቲ እና በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተሞች መሆኑን ገልጸዋል።

በየካ እና በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተሞች የሕፃናት ብቻ ቀብር የሚፈጸም ሲሆን፣ በተለይም በጉለሌ ክፍለ ከተማ ላይ ከፍተኛ የሥራ ጫና እንዳለ ገልጸዋል።

ፖሊስ ከመንገድ ያነሳቸውን ጨምሮ አስከሬኖች ወደ ሆስፒታል ከሄዱ በኋላ፣ ሆስፒታሎቹ ፈላጊና ጠያቂ የሌላቸው መሆኑን አረጋግጠው ቦታ ሲጠባቸው ይነሱልን ብለው በደብዳቤ ሲጠይቁን የቢሯችን ሠራተኞች ሂደቱን አሟልተው ያነሳሉ፣ ይቀብራሉም ብለዋል።

በሪፖርቱ ላይ የሕፃናት ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ መብዛቱ አሳሳቢ መሆኑን የጠቀሱት የቡድን መሪው፣ እናቶች ልጆቻቸውን በሆስፒታል ወልደው ጥለው የመጥፋት ሁኔታዎች በብዛት እንደሚስተዋሉ ገልጸዋል።

ለዚህም እንደ ዋና ምክንያት የቅድመ ወሊድና ድህረ ወሊድ ክትትል አለመኖር በቂ ግንዛቤና ትምህርት አለማግኘትን መሆኑን አብራርተዋል።

አክለውም ፤ወደፊት ችግሩን ለመቅረፍ በሴቶች ላይ ትኩረት አድርጎ መሥራት፣ በትምህርት ቤቶችና በተለያዩ መድረኮች የግንዛቤ ፈጠራ ሥራዎችን በስፋት ማከናወን እንደሚገባ አሳስበዋል።

የከተማዋ የሕዝብ ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ፣ አሁን በስድስት ክፍለ ከተሞች ላይ ብቻ የተወሰነውን ይህንን አገልግሎት ወደሌሎችም ክፍለ ከተሞች በማስፋፋት የሥራ ጫናውን ማቃለል እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በ ወልደሐዋርያት ዘነበ

,_ድምጽ

ምስል በ AI የበለፀገ

29/05/2026

ሳቁልኝ
ሰውየው የሚስቱን ድመት በጣም ይጠላው ነበር….አንድ ቀን ሚስቱ ሳታየው ድመቱን አውጥቶ ለመጣል ይወስናል...

በጠዋት ተነስቶም ድመቱን 20 ኪ.ሜ ያህል ራቅ አድርጎ ይጥልና በደስታ ይመለሳል እቤቱ ሲደርስ ግን ድመቱ ሶፋ ላይ ተኝቶ ያገኘዋል...

በነጋታው ጠዋት ይነሳና ድመቱን 40 ኪ.ሜ ራቅ አድርጎ ጥሎት ተመለሰ እቤት ሲደርስ ድመቱ እንደ ትላንቱ ሶፋ ላይ ተኝቶ ያገኘዋል

በየቀኑ ራቅ ራቅ ወዳለ ቦታ እየጣለው ይመጣል ድመቱ ግን ሁሌም ቀድሞት እቤት እንደገባ ነው::

በመጨረሻም በጣም ይመረውና ድመቱ አያውቀውም ብሎ ወደሚያስብበት ሩቅ ቦታ ሊጥለው ይወስናል

ብዙ ኪሎሜትሮችን ከተጓዘ በኃላ ወደ ቀኝ ታጠፈ ከዛ ወደ ግራ ከዛ ወንዙን ተሻግሮ ወደ ቀኝ ድጋሜ ወደ ግራ አሁንም ጥቂት ተጉዞ ወደ ቀኝ እንዲ እንዲ እያለ

የሆነ ቦታ ሲደርስ አሁን ተገላገልኩ ብሎ ድመቱን ይለቀዋል…. ከሰሀታት በኃላ ሰውየው ሚስቱጋ ደውሎ “ሆዴ ድመቱ ቤት አለ እንዴ?”

ሚስት:” አዎ ምነው….? “
ሰውየው “እስቲ አንዴ አቅሪቢልኝ መንገድ ጠፍቶብኝ ነው”
😂😂😂😂
መልካም በዓል

24/02/2026
24/02/2026

#ፈጣሪ እንዴት ይታረቀን? 😭😭😭
ልጅ ወልዶ እንደቆሻሻ እንዲህ በየመንገዱ መጣል ምን ይሉታል።

24/02/2026

Address

Addis Ababa

Telephone

+251911484405

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when BBETE posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share